2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

About Us

Our Mission, Vission and Core Values

Vision

To Be a Leading Trade Union in East Africa by 2025

Mission

Our Mission is to provide collective voice to the employees’ of CBE and enhance integrated action to build and sustain a healthy and safe working environment and respectful workplace where its members deliver the bank’s services with professional pride

Core Values

- Members’ right - Organizational peace - Professionalism - Integrity and Accountability - Diversity and solidarity - Empowerment

Our Objective

- Exert more effort to the realization of vision mission, objective and goals of the bank. - Assure proper protection and enforcement of rights privileges of the employees in line with the national and international labor conventions and terms and conditions stipulated in the collective agreement in force; - Protect the employees against unfair exploitation of labor and improper utilization of efforts and skills. - Support the members during the time of financial distress and unlawful eviction/ dismissal from job. - Promote customer satisfaction via employees’ satisfaction. - Raise awareness on the rights and duties of employees in line with the existing national laws, international labor conventions, and human resources principles (CBE Labor Informer).

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ታሪክ

ኢትዮጵያ ውስጥ የሠራተኞች በማሕበር የመደራጀት መብት በሕግ የተደነገገዉ በአዋጅ ቁጥር 49/1954 ቢሆንም ይህን በተግባር ለመፈፀም ግን ከፍተኛ ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ እና በጅቡቲ መስመር ባቡር ሠራተኞች የተጀመረዉ የመደራጀት ትግል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞችም በከፍተኛ ፈተና ውስጥ ማለፉን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በድብቅ በሻይ ቤቶች፣ በግለሰብ ቤቶች እና በት/ቤቶች (በተለይ ተግባረዕድ ኮሌጅ) ውስጥ ውይይቶችን እና የመደራጀት እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ የነበሩ የባንኩ ሠራተኞች ነሐሴ 8 ቀን 1959 ዓ.ም በ500 አባላት እና 1200 በሚሆን ካፒታል “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር”ን በይፋ መሠረቱ፡፡ ይህ የተመሠረተዉ ማሕበር ህጋዊ ዕዉቅና እንዲሰጠዉ ወዲያዉኑ የተጠየቀ ቢሆንም ዕዉቅና የተሰጠዉ ግን ከ3 ወራት በኋላ ህዳር 28 ቀን 1960 ዓ.ም ነበር፡፡ ማሕበሩ እንደ ተቋቋመ የመጀመሪያ ተግባሩ የነበረዉ ሕብረት ስምምነት መደራደር ነበር፡፡ በሕብረት ድርድሩ ወቅት ማሕበሩ እና የባንኩ ማኔጅመንት ያልተስማሙባቸውን በርካታ አብይ ጉዳዮች ስለነበሩ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ እንዲታይለት ማሕበሩ አቤቱታ አቀረበ፡፡ ሆኖም በቦርዱ አሸማጋይነት እየታዩ የነበሩት የድርድር ነጥቦች መቋጫ ሳያገኙ ከስድስት ወራት በላይ ስለቆዩ እና የባንኩ ማኔጅመንት የሁለቱን ወገኖች ግንኙነት የሚያሻክሩ እና ውጥረቱን የሚያባብሱ ድርጊቶችን እየፈፀመ ስለነበረ መንግስት ጣልቃ ገብቶ መፍትሄ እንዲያበጅ ማሕበሩ እንደገና ለመንግስት አቤቱታዉን አቅርቦ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ባለማግኘታቸዉ እና ነገሩን በሠላም ለመጨረስ የተደረገዉ ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ ኢንባሠማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞችን በማስተባበር እና ከኢሠአማ(የኢትዮጵያ ሠራተኞች አንድነት ማሕበር) የዛሬዉ ኢሠማኮ ጋር በመነጋገር ከነሐሴ17 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 1965 ዓ.ም ለ9 ቀን የቆየ የሥራ ማቆም እርምጃ ወሰደ፡፡ በኋላም መንግስት ጣልቃ ገብቶ ድርድሩ እንዲካሄድ በማድረግ ህዳር 10 ቀን 1966 ዓ.ም (ማሕበሩ ከተቋቋመ ከ6 ዓመታት በኋላ) በባንኩ እና የሠራተኛ ማሕበሩ መካከል የመጀመሪያው የሕ/ስምምነት ተፈረመ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሠራተኞች የመደብ ትግል ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴን መንግስት ከሥልጣን ለማውረድ የድርሻዉን ተወጥቷል፡፡ የተካሄደውን የህዝብ አመፅ ተከትሎ ቀደም ሲል የኢሠአማ ጠቅላይ ምክር ቤት በአባሎቹ ላይ የሚደርሰውን ችግር ለብዙ ጊዜ ሲያሰማ ቆይቶ ባለመደመጡ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ አባሎቹ በሙሉ ሥራ እንዲያቆሙ ኢሠአማ በወሰነው መሠረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞችም እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ከየካቲት 27 እስከ የካቲት 30 ድረስ (ለ4 ቀን የቆየ) የሥራ ማቆም እርምጃ አድርጓል፡፡  በማሕበሩ ውስጥ የነበሩ አበይት ለዉጦች፡-  ህዳር 1968 ዓ.ም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 64/68 መታወጁን ተከትሎ ማሕበሩም በዚሁ አዲስ አዋጅ መሠረት ሐምሌ 30 ቀን 1968 ዓ.ም በአዲስ መልክ እንዲመዘገብ ተደረገ፤  ሰኔ 24 ቀን 1972 ዓ.ም የኢ.ን.ባ ሠራተኞች ማሕበር ከአዲስ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ጋር ተዋሃደ፣  ኢህአዴግ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የተቋቋመው የሽግግር መንግስት ባወጣው የውስጥ መመሪያ በአዋጅ ቁጥር 64/68 መሠረት ተቋቁመዉ ከሐምሌ 27 ቀን 1983 ዓ.ም በፊት ያሉ የሠራተኛ ማሕበራት በሙሉ እንዲፈርሱና በአዲስ መልክ እንዲደራጁ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡ ኢንባሠመማ በመመሪያዉ መሠረት ጥቅምት 15 ቀን 1984 ዓ.ም በአዲስ መልክ ተቋቋመ፡፡  በአዲስ መልክ የተቋቋመው የሠራተኞች ማሕበር ጠቅላይ ም/ቤት ጥቅምት 28 ቀን 1984 ዓ.ም ለባንኩ ማኔጅመንት በፃፈው ደብዳቤ አማካይነት ኢኮኖሚ ነክ ጥያቄዎችን አቀረበ፣ ይሁንና ጥያቄዎች በተለያዩ የመንግስት አካላት ዘንድ እየተድበሰበሰ ምላሽ ባለማግኘታቸው የባንኩ ሠራተኞች ከታህሳስ 2 እስከ ታህሳስ 13 ቀን 1984 ዓ.ም ድረስ (ለ12 ቀናት የቆየ) የሥራ ማቆም እርምጃ ወሰደ፡፡  በ1984 ዓ.ም በተወሰደዉ የሥራ ማቆም እርምጃ የደረሰዉ ጉዳት፡-  መንግስት አጠቃላይ የባንኩን ሠራተኞች እና የማሕበሩን ጠቅላይ ም/ቤት አባላት ከታህሳስ 04 ቀን 1984 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ አባርሬያለሁ በማለት ወሰነ  በተጨማሪ የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሠራተኛ ማሕበሩ በሕግ ይፍረስልኝ በማለት ለሽግግር መንግስቱ የሠራተኛ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ክስ አቀረበ  ማሕበሩ በፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ ደግሞ ታህሳስ 14 ቀን 1984 ዓ.ም የከፍተኛ ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችሎት ላይ ባንኩ ሁሉንም ሠራተኞች ወደ ሥራ መልሻለሁ፤ ነገር ግን 52ቱ የጠቅላይ ም/ቤቱ አባላት ወደ ሥራ አይመለሱም አለ፣  ነሐሴ 15 ቀን 1985 ዓ.ም የሠራተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ወደ ሥራ ያልተመለሱትን የማሕበሩን ጠ/ም/ቤት አባላት ወደ ሥራ ለማስመለስ ይቻል ዘንድ ከመንግስት ጋር የሚደራደር አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቋመ፣  የሽግግር መንግስቱ የሠራተኛ ማሕበሩን በአዲስ መልክ ካቋቋመ በኋላ ወደ ሥራ ያልተመለሱት የማሕበሩ የቀድሞ ጠቅላይ ም/ቤት አባላት ወደ ሥራ እንዲመለሱ የገባውን ቃል መሠረት በማድረግ ታህሳስ 6 ቀን 1986 ዓ.ም አዳዲስ የጠቅላይ ም/ቤትና የአመራር አባላት ተመረጡ፣  መጋቢት 01 ቀን 1986 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ አማካይነት ከዚህ ቀደም ወደ ሥራ እንዳይመለሱ ተከልክለው ከነበሩት 52 የሠራተኛ ማሕበሩ የጠ/ምር ቤት አባላት መካከል 46ቱ ከየካቲት 22 ቀን 1986 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለሱ የተፈቀደና የተቀሩት 6 አባላት (የሥራ አስፈፃሚ አባላት) ግን ወደ ሥራ እንደማይመለሱ መወሰኑ ተገለፀ፣  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛም ወደ ሥራ ሳይመለሱ የቀሩ 6ቱ አመራሮች ሌላ ሥራ እስከሚያገኙ ድረስ ከደመወዙ እየቆረጠ ለ27 ወራት ሙሉ ደመወዛቸዉን እየከፈላቸዉ መቆየቱን ታሪክ ያስታዉሰናል፡፡  ሕብረት ስምምነቶች፡- በባንኩ እና በሠራተኛ ማሕበሩ መካከል እስከ አሁን 13 የሕብረት ስምምነቶች ተፈርሟል፤ በጥሩ መግባባት ወቅታቸዉን ጠብቀዉ የተፈረሙት ግን ጥቂቶች ናቸዉ፡፡ በአጠቃላይ የተካሄዱ ድርድሮች እና የተፈረሙበት ወቅት እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡ 1ኛዉ ሕ/ስምምነት ህዳር 10 ቀን 1966 ዓ.ም 2ኛዉ ሕ/ስምምነት መስከረም 12 1970 ዓ.ም 3ኛዉ ሕ/ስምምነት መጋቢት 1972 ዓ.ም 4ኛዉ ሕ/ስምምነት ሐምሌ 19 ቀን 1974 ዓ.ም 5ኛዉ ሕ/ስምምነት 1976 ዓ.ም 6ኛዉ ሕ/ስምምነት ሰኔ 27 ቀን 1979 ዓ.ም 7ኛዉ ሕ/ስምምነት ሐምሌ 4 ቀን 1981 ዓ.ም 8ኛው ሕ/ስምምነት የካቲት 16 ቀን 1986 ዓ.ም 9ኛው ሕ/ስምምነት ጥቅምት 28 ቀን 1995 ዓ.ም 10ኛው ሕ/ስምምነት መጋቢት 26 ቀን 1998 ዓ.ም 11ኛው ሕ/ስምምነት መጋቢት 22 ቀን 2002 ዓ.ም 12ኛው ሕ/ስምምነት የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም 13ኛው ሕ/ስምምነት ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈርመዋል፡፡  የማሕበሩ አሁናዊ ሁኔታዎች (ከ2012 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም) የማሕበሩ አሁናዊ ቁመና ማሕበሩ አሁን ላይ 28,256 (ሃያ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት) አባል ሠራተኞች (ምሁራን) ያለዉ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማሕበራት የተሻለ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር እ.ኤ.አ በጁን 30 ቀን 2021 በአጠቃላይ 173,669,682.14( አንድ መቶ ሰባ ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ከአስራ አራት ሳንቲም) ያክል ጥሬ ገንዘብ፣ አንድ ባለ 4 ወለል ሕንፃ እና 3 መኪኖች ያለዉ ትልቅ ተቋም ነዉ፡፡ ከዚህም አንጻር የማሕሩ ተደማጭነት እንዲጨምር እና በማሕበሩ እና በባንኩ ወይም በመንግሰት አካላት እንዲሁም ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በዕዉቀት እና በመርህ ላይ የተመሠረት ጤናማ ግንኙነት (win-win approach) እንዲፈጠር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በባንኩ በኩል ቢያንስ ሠራተኛዉን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ከመወሰናቸዉ በፊት “ማሕበሩ ምን ይላል?” የሚል አመለካከት እንዲያድርባቸዉ ተደርጓል:: የሠራተኛዉን የመብት እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ከማስከበር አንፃር  በ2010 ዓ.ም ባንኩ የተገበረዉ አዲስ መዋቅር አንደኛ የሠራተኛዉ ምደባ ላይ ከፍተኛ የአሰራር ግድፈት ስለነበረዉ እና ሁለተኛ ሠራተኛዉ እና ማሕበሩ ሲጠይቁ የቆዩትን የደመወዝ ማስተካከያ ሳያካትት ስለመጣ ከፍተኛ ቅሬታ ገጥሞት ነበር፡፡ በመሆኑም የማሕበሩ ሥራ አስፈፃሚ እና የም/ቤት አባላት ባደረጉት እንቅስቃሴዎች ማለትም፡- አዲስ አበባ ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር በኢግዚብሽን ማእከል ስብሰባ በማድረግ እስከ ሥራ ማቆም የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ መቀስቀስ፣ የተወሰኑ ጉዳዮችን ወደ ፍ/ቤት በመውሰድ እና ከመላዉ ሠራተኛ የሥራ ማቆም እርምጃ ፊርማ በማሰባሰብ እና ለባንኩ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ባንኩ ለድርድር እንዲቀመጥ ተደርጎ የሚከተሉት ውጤቶች ተገኝተዋል፡-  አዲስ የደመወዝ ማስተካከያ ስኬል ተጠንቶ እስኪመጣ ድረስ የቤት ኪራይ አበል፣ የኑሮ ውድነት/የበረሀ አበል፣ የሺፍቲንግ ክፍያ እና የገንዘብ ጉድለት መጠባበቂያ ክፍያ ለረጅም ጊዜ የቆዩ እና የወቅቱን ገበያ ያላገናዘቡ በመሆናቸዉ እንዲስተካከል ተደርጓል፤  ተግባራዊ በሆነዉ አዲስ መዋቅር ላይ በተደረገዉ የሠራተኞች ምደባ ምክንያት የተፈጠረዉ ከፍተኛ የሠራተኞች ቅሬታ እንዲፈታ ከባንኩ እና ከማሕበሩ የተወጣጣ የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲያጠና እና መፍትሄ እንዲያስቀምጥ ተደርጓል፤  የሠራተኞች የደረጃ እድገት ውድድር ፈተና 50% እና የሥራ አፈጻጸም ምዘና (PMS) 50% በማድረግ ሲሠራበት የቆየዉ በዛን ጊዜ በነበረዉ 12ኛዉ ሕ/ስምምነት መሠረት የሥራ አፈጻጸም 50%፣ ትምህርት 2%፣ የሥራ ልምድ 10%፣ የአገልግሎት ዘመን 15% እና ለጽሁፍ ወይም የተግባር ፈተና 23% እንዲሆን ተደርጓል፡፡  ባንኩ እንደገና በ2012 ዓ.ም ተግባራዊ ባደረገዉ አዲሱ መዋቅር ምክንያት ከ 7,500 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች ከደረጃቸዉ ዝቅ ተደርገዉ የነበረ ሲሆን በሕግ እና በውይይት ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ ወደ ደረጃቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡  ከ2012 ጀምሮ ተቋርጦ እና በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች ታጥረዉ የነበሩ የሠራተኞች ብድሮች 13ኛዉ ሕ/ስምምነት ላይ እንዲገቡ እና ተስተካክለዉ እንዲፈቀድ ተደርጓል፤  በ2013 በብዛት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እና በሌሎች በተወሰኑ ከተሞች የሚሰሩ 410 የሚሆኑ አባል ሰራተኞች ከመርከብ ጭነት ክፍያ ጋር ተያይዞ ከስራ ታግደው የነበሩ ሲሆን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት እና ድርድር ከ 4 ሰራተኞች በስተቀር ሁሉም ሰራተኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፤  በ2013 ከ11 ዓመታት በላይ ሳይታደስ የቆየው 12ኛው የሕብረት ስምምነት አዳዲስ ፓኬጆችን ጨምሮ ሠራተኛውን እና ባንኩን በሚጠቅም መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ አልቆ 13ኛው የሕብረት ስምምነት ተፈርሟል።  በ2014 ሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት እና 13ኛዉ ሕ/ስምምነት በሚል ርዕስ የቅርንጫፍ ተወካዮችን እና ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ ለተለያዩ የባንኩ ማሕበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በስፋት ተሰጥቷል፡፡ የማሕበሩን ተቋማዊ አቅም ከማሳደግ አንፃር  የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እንዲዘጋጅ ተደርጎ እና በማሕበሩ ም/ቤት ፀድቆ ሥራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፤  የማሕበሩን ሕገ-ደንብ በማሻሻል ማኅበሩን የሚመጥን አደረጃጀት እና የሠራተኞች ዉክልና እንዲኖር ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት፡-  የማሕበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንደገና እንዲቋቋም ተደርጓል፤  ክትትልና ድጋፍ እንዲኖር በየተጠሪ ጽ/ቤቱ መማክርት እንዲቋቋም ተደርጓል፤  የማሕበሩ ሥራ አስፈጻሚ በዘርፍ እንዲደራጅ ተደርጓል፤  በየቅርንጫፉ ወይም የሥራ ክፍሉ የሚመረጡ የሠራተኞች ተወካዮች 3 እንዲሆኑ እና ሰብሳቢዉ የጠቅላላ ጉባዔ አባል እንዲሆን ተደርጓል፤  የጠቅላይ ም/ቤቱ፤ ኦዲት ኮሚቴዉ፣ የመድን ኮሚቴዉ እና የተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ተግባራት በዝርዝር እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡  የአባላት ድጋፍ መመሪያ እና የፋይናንስ፣ የግዥ እና የንብረት አስተዳደርን መመሪያን ጨምሮ ከ 10 በላይ መመሪያዎች ተዘጋጅተዉ በም/ቤቱ ፀድቀዉ ሥራ ላይ እንዲዉሉ ተደርጓል፡፡ የማኅበሩን የፋይናንስ አሠራር ወጥ ለማድረግ እና የማኅበሩን ሀብት ለመጠበቅ የፋይናንስ መመሪያ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ በሐበሻ ቢራ፣ ከኢንተርናሽናል የልብ እና ልብነክ ህክምና ማዕከል (ICMC) አክሲዮን በመግዛት የማሕበሩን ገቢ ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል፡፡ ማሕበሩ ማሕበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ማሕበራችን እንደ ተቋምም ሆነ አባል ሠራተኞችን በማንቀሳቀስ መንግስት እና ሕዝብ በሚያቀርቡለት ሀገራዊ ጉዳዮችም ሆነ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሚያቀርቡለት የድጋፍ ጥያቄዎች ላይ በስፋት በመሳተፍ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል፡፡ በዚሁ አግባብ ለኮቪድ-19 መከላከል፣ በም/ቤት ስብሰባዎች ላይ ደም በመለገስ፣ ለኢትዮጰያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል፣ ለመቄዶኒያ የአረጋዉያን እና የአዕምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል፣ አዋሽ አርባ ከተማ ለሚገኘው የአረጋውያን እና የህፃናት መርጃ ማዕከል እና ለሌሎች ተቋማት ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡  በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች፡- 1. ሠራተኛዉ በባንኩ የቦርድ አመራር ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖረዉ ማድረግ 2. የኢትዮጵያ ሠራተኞች የመብት ትግል ከተቋም ደረጃ ወቶ በፖለቲካዉ መድረክ ጎልቶ እንዲወጣ ከኢሠማኮ ጋር መሥራት 3. የማሕበሩን ጥሬ ገንዘብ ወደ ቋሚ ሀብት እና ኢንቨስትመንት መቀየር

የማሕበሩ አሁናዊ ሁኔታዎች (ከ2012 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም)

የማሕበሩ አሁናዊ ቁመና ማሕበሩ አሁን ላይ 28,256 (ሃያ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት) አባል ሠራተኞች (ምሁራን) ያለዉ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማሕበራት የተሻለ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር እ.ኤ.አ በጁን 30 ቀን 2021 በአጠቃላይ 173,669,682.14( አንድ መቶ ሰባ ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ከአስራ አራት ሳንቲም) ያክል ጥሬ ገንዘብ፣ አንድ ባለ 4 ወለል ሕንፃ እና 3 መኪኖች ያለዉ ትልቅ ተቋም ነዉ፡፡ ከዚህም አንጻር የማሕሩ ተደማጭነት እንዲጨምር እና በማሕበሩ እና በባንኩ ወይም በመንግሰት አካላት እንዲሁም ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በዕዉቀት እና በመርህ ላይ የተመሠረት ጤናማ ግንኙነት (win-win approach) እንዲፈጠር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በባንኩ በኩል ቢያንስ ሠራተኛዉን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ከመወሰናቸዉ በፊት “ማሕበሩ ምን ይላል?” የሚል አመለካከት እንዲያድርባቸዉ ተደርጓል:: የሠራተኛዉን የመብት እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ከማስከበር አንፃር  በ2010 ዓ.ም ባንኩ የተገበረዉ አዲስ መዋቅር አንደኛ የሠራተኛዉ ምደባ ላይ ከፍተኛ የአሰራር ግድፈት ስለነበረዉ እና ሁለተኛ ሠራተኛዉ እና ማሕበሩ ሲጠይቁ የቆዩትን የደመወዝ ማስተካከያ ሳያካትት ስለመጣ ከፍተኛ ቅሬታ ገጥሞት ነበር፡፡ በመሆኑም የማሕበሩ ሥራ አስፈፃሚ እና የም/ቤት አባላት ባደረጉት እንቅስቃሴዎች ማለትም፡- አዲስ አበባ ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር በኢግዚብሽን ማእከል ስብሰባ በማድረግ እስከ ሥራ ማቆም የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ መቀስቀስ፣ የተወሰኑ ጉዳዮችን ወደ ፍ/ቤት በመውሰድ እና ከመላዉ ሠራተኛ የሥራ ማቆም እርምጃ ፊርማ በማሰባሰብ እና ለባንኩ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ባንኩ ለድርድር እንዲቀመጥ ተደርጎ የሚከተሉት ውጤቶች ተገኝተዋል፡-  አዲስ የደመወዝ ማስተካከያ ስኬል ተጠንቶ እስኪመጣ ድረስ የቤት ኪራይ አበል፣ የኑሮ ውድነት/የበረሀ አበል፣ የሺፍቲንግ ክፍያ እና የገንዘብ ጉድለት መጠባበቂያ ክፍያ ለረጅም ጊዜ የቆዩ እና የወቅቱን ገበያ ያላገናዘቡ በመሆናቸዉ እንዲስተካከል ተደርጓል፤  ተግባራዊ በሆነዉ አዲስ መዋቅር ላይ በተደረገዉ የሠራተኞች ምደባ ምክንያት የተፈጠረዉ ከፍተኛ የሠራተኞች ቅሬታ እንዲፈታ ከባንኩ እና ከማሕበሩ የተወጣጣ የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲያጠና እና መፍትሄ እንዲያስቀምጥ ተደርጓል፤  የሠራተኞች የደረጃ እድገት ውድድር ፈተና 50% እና የሥራ አፈጻጸም ምዘና (PMS) 50% በማድረግ ሲሠራበት የቆየዉ በዛን ጊዜ በነበረዉ 12ኛዉ ሕ/ስምምነት መሠረት የሥራ አፈጻጸም 50%፣ ትምህርት 2%፣ የሥራ ልምድ 10%፣ የአገልግሎት ዘመን 15% እና ለጽሁፍ ወይም የተግባር ፈተና 23% እንዲሆን ተደርጓል፡፡  ባንኩ እንደገና በ2012 ዓ.ም ተግባራዊ ባደረገዉ አዲሱ መዋቅር ምክንያት ከ 7,500 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች ከደረጃቸዉ ዝቅ ተደርገዉ የነበረ ሲሆን በሕግ እና በውይይት ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ ወደ ደረጃቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡  ከ2012 ጀምሮ ተቋርጦ እና በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች ታጥረዉ የነበሩ የሠራተኞች ብድሮች 13ኛዉ ሕ/ስምምነት ላይ እንዲገቡ እና ተስተካክለዉ እንዲፈቀድ ተደርጓል፤  በ2013 በብዛት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እና በሌሎች በተወሰኑ ከተሞች የሚሰሩ 410 የሚሆኑ አባል ሰራተኞች ከመርከብ ጭነት ክፍያ ጋር ተያይዞ ከስራ ታግደው የነበሩ ሲሆን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት እና ድርድር ከ 4 ሰራተኞች በስተቀር ሁሉም ሰራተኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፤  በ2013 ከ11 ዓመታት በላይ ሳይታደስ የቆየው 12ኛው የሕብረት ስምምነት አዳዲስ ፓኬጆችን ጨምሮ ሠራተኛውን እና ባንኩን በሚጠቅም መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ አልቆ 13ኛው የሕብረት ስምምነት ተፈርሟል።  በ2014 ሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት እና 13ኛዉ ሕ/ስምምነት በሚል ርዕስ የቅርንጫፍ ተወካዮችን እና ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ ለተለያዩ የባንኩ ማሕበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በስፋት ተሰጥቷል፡፡ የማሕበሩን ተቋማዊ አቅም ከማሳደግ አንፃር  የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እንዲዘጋጅ ተደርጎ እና በማሕበሩ ም/ቤት ፀድቆ ሥራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፤  የማሕበሩን ሕገ-ደንብ በማሻሻል ማኅበሩን የሚመጥን አደረጃጀት እና የሠራተኞች ዉክልና እንዲኖር ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት፡-  የማሕበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንደገና እንዲቋቋም ተደርጓል፤  ክትትልና ድጋፍ እንዲኖር በየተጠሪ ጽ/ቤቱ መማክርት እንዲቋቋም ተደርጓል፤  የማሕበሩ ሥራ አስፈጻሚ በዘርፍ እንዲደራጅ ተደርጓል፤  በየቅርንጫፉ ወይም የሥራ ክፍሉ የሚመረጡ የሠራተኞች ተወካዮች 3 እንዲሆኑ እና ሰብሳቢዉ የጠቅላላ ጉባዔ አባል እንዲሆን ተደርጓል፤  የጠቅላይ ም/ቤቱ፤ ኦዲት ኮሚቴዉ፣ የመድን ኮሚቴዉ እና የተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ተግባራት በዝርዝር እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡  የአባላት ድጋፍ መመሪያ እና የፋይናንስ፣ የግዥ እና የንብረት አስተዳደርን መመሪያን ጨምሮ ከ 10 በላይ መመሪያዎች ተዘጋጅተዉ በም/ቤቱ ፀድቀዉ ሥራ ላይ እንዲዉሉ ተደርጓል፡፡ የማኅበሩን የፋይናንስ አሠራር ወጥ ለማድረግ እና የማኅበሩን ሀብት ለመጠበቅ የፋይናንስ መመሪያ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ በሐበሻ ቢራ፣ ከኢንተርናሽናል የልብ እና ልብነክ ህክምና ማዕከል (ICMC) አክሲዮን በመግዛት የማሕበሩን ገቢ ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል፡፡ ማሕበሩ ማሕበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ማሕበራችን እንደ ተቋምም ሆነ አባል ሠራተኞችን በማንቀሳቀስ መንግስት እና ሕዝብ በሚያቀርቡለት ሀገራዊ ጉዳዮችም ሆነ ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሚያቀርቡለት የድጋፍ ጥያቄዎች ላይ በስፋት በመሳተፍ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል፡፡ በዚሁ አግባብ ለኮቪድ-19 መከላከል፣ በም/ቤት ስብሰባዎች ላይ ደም በመለገስ፣ ለኢትዮጰያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል፣ ለመቄዶኒያ የአረጋዉያን እና የአዕምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል፣ አዋሽ አርባ ከተማ ለሚገኘው የአረጋውያን እና የህፃናት መርጃ ማዕከል እና ለሌሎች ተቋማት ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡  በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች፡- 1. ሠራተኛዉ በባንኩ የቦርድ አመራር ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖረዉ ማድረግ 2. የኢትዮጵያ ሠራተኞች የመብት ትግል ከተቋም ደረጃ ወቶ በፖለቲካዉ መድረክ ጎልቶ እንዲወጣ ከኢሠማኮ ጋር መሥራት 3. የማሕበሩን ጥሬ ገንዘብ ወደ ቋሚ ሀብት እና ኢንቨስትመንት መቀየር

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማኅበር መዋቅር

Our Services

LEGAL SUPPORT

The central objective of the Union is to negotiate terms and conditions of work for its members with bank and watch out the proper enforcement of the negotiation results- mainly the Collective Agreement. Thus, if any member needs any work-place related legal advice the Union provides the same through its professional “Legal Advice "or through other officials free of charge. Moreover, if any representative is hurt because of his/her Union representation, the Union goes up to paying his/her monthly salary for one year, and hires prosecutor to deal with the issue representing the victim.

FINANCIAL SUPPORTS FOR MEMBERS

1. Patient visit:- the Union’s representatives visit a member who is hospitalized 2. Fell-up Salary During Sick:- fulfilling a member’s salary deducted due to longer sick leave 3. Oversea Treatment:- support when a member is referred to abroad for medical treatment 4. Overtake sick leave is a support provided when a member salary is being deducted due to longer sick leave 5. Detention:-Support if a member is imprisoned for any reason 6. Suspension:- support if a member is suspended from work for any reason 7. Termination:-Support based on service year at the bank, when a member terminates his/her contract with the bank upon owns interest or, when the bank fired the member for any reason 8. Pensioned:- Financial and certificate awards when a member and a manager gets retired from the bank 9. Disaster: - Support if a natural or manmade ruin encountered a member or family or property 10. Deceased:-at the end if a member dies, the union pays for funeral expenses or grants money to heiress

EMPLOYEES CLUBS SUPPORT

The Union provides financial grants for employees’ clubs at all level from its own budget at every five years based on their population & temperature of the town in which they are in; and the Unionadministers the budget yearly allocated from the bank in the way it benefits employees properly.

HEALTH RELATED SUPPORT

HEALTH RELATED SUPPORT The union in collaboration with the bank collects contribution from the bank’s community and relocates the fund to victim employees or their families as a result of HIV/AIDS, Cancer, accident or any other severe damages.

More About Services

Executive Committee Members

Audit Committee Members

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000