2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

Article

አሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የተደረጉ ማሻሻያዎች አዲስ የተጨመሩ አንቀጾች እና ሃሳቦች በጥቂቱ

ትርጓሜ - ከዚህ ቀደም ከነበሩት ትርጓሜዎች በተጨማሪ አዲሱ አዋጅ ስለወሲባዊ ትንኮሳ ፤ ወሲባዊ ጥቃት፤ በሰራተኞች ማካከል ልዩነት ስለማድረግ እና ሌሎች ተጨማሪ ትርጓሜዎችን አካቷል፡፡ የህጉ (የአዋጁ) ተፈጻሚነት ወሰን - ከቀድሞ አዋጅ በተለየ መልኩ ከቅጥር ግንኙነት በተጨማሪ በምልመላ ሂዲት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል በማለት በአንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ አካቷል፡፡ የተከለከለ ድርጊት - በአንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2(8) ሰራተኞች ከአሰሪው ፍቃድ ሳያገኝ በስራ ሰዓት ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ተግባር መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የሙከራ ጊዜ - በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 11(3) መሰረት የሚከራ ጊዜው ሰራተኛው ስራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ለስልሳ የስራ ቀኖች ሊሆን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ስለማቋረጥ (በአሰሪው) - አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1(ሀ) መሰረት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር በጠቅላላው ለስምንት ጊዜያት የስራ ሰዓት አለማክበር እና አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1(ለ) የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት ከስራ መቅረት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ለማቋረጥ በቂ ምክንያት እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ማቋረጥ (በሰራተኛው) - በአንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 1(ለ) መሰረት በአሰሪው ወይም በስራ መሪው የወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት የተፈጸመበት ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውሉን ማቋረጥ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ ስለስራ ስንብት ክፍያና ስለካሳ - በአንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1(መ) ሰራተኛው በአሰሪ ወይም ከስራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የተፈጸመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሰራተኛ እንደተፈጸመ ሪፖርት ተደርጎለት አሰሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሰራተኛው የስራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ የስራ ስንብት ክፍያ ሊከፈለው እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡ ስለካሳ ክፍያ (በአሰሪው) - በአንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 2 በተደነገገው መሰረት በአንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 1(ለ) መሰረት  በህግ ከተደነገገው ምክንያት ውጪ በአሰሪው አነሳሽነት የስራ ውሉ ሲቋረጥ ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የዘጠና ቀን ደመወዙን በካሳ መልክ ያገኛል፡፡ ስለካሳ ክፍያ (በሰራተኛው) - በተሻረው አዋጅ ላይ በግልጽ የአከፋፈሉን ሁኔታ ባይደነገግም በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ሰራተኛው ስለማስጠንቀቂያ የተጠቀሱትን አስፈላጊ ሁኔታዎች ያላሟላ ሰራተኛ ለአሰሪው የ30 ቀን ደመወዙን ለአሰሪው በካሳ መልክ መክፈል እንዳለበት እና ለሰራተኛው ሊከፈል ከሚችሉ ክፍያዎች ላይ ተቀናሽ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ የትርፍ ሰአት ስራ አከፋፈል - አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ሀ- ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰአት የሚሰራ የትርፍ ሰአት ክፍያ ለመደበኛ ስራ በሰዓት የሚከፈለውን ደመወዝ በአንድ ተኩል ተባዝቶ ለ- ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት የሚሰራ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ለመደበኛ ስራ በሰዓት የሚከፈለውን ደመወዝ በአንድ ሶስት አራተኛ ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡ የሳምንት የዕረፍት ጊዜን በተመለከተ - አንቀጽ 69 ንዑስ አንቀጽ 4 በተደነገገው መሰረት ሰራተኛው በስራው ባህሪ ምክንያት የሳምንቱን የዕረፍት ቀን በመጠቀም ያልቻለ እንደሆነ አሰሪው ለሰራተኛው በወር ውስጥ 4 ቀናት ዕረፍት እንዲያገኝ ማድረግ አለበት፡፡ የዓመት ፍቃድ መጠን - አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ለመጀመሪያ የአንድ አመት አገልግሎት 16 ቀን እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሁለት የአገልግሎት አመታት አንድ የስራ ቀን እየጨመረ ይሰጣል፡፡ ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፍቃድ - አንቀጽ 81 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ሰራተኛው የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት ሶስት ተከታታይ ቀናት ፍቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም በአንቀጽ 81 ንዑስ አንቀጽ 3 ሰራተኛው ልዩ እና አሳሳቢው ሁኔታ ሲያጋጥመው ለአምስት ተከታታይ ቀናት ያለክፍያ የማግኘት መብት አለው፡፡ ሆኖም በዚህ ረገድ የሚሰጠው ፈቃድ በበጀት ዓመቱ ከሁለት ጊዜ ሊበልጥ አይችልም፡፡ የወሊድ ፍቃድ - በአንቀጽ 88 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ከመውለድዋ በፊት አንድ ወር እንዲሁም ከወለደች በኃላ ሶስት ወር ይሰጣታል፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Categories

Recent Articles

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000