2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የማሕበራችን አስቸኳይ እና 62ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ተጠናቀቀ

ለሁለት ቀናት ተጠርቶ ሁለት ቀን ተኩል የፈጀዉ ይህ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ዉሣኔዎችንና አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ 1ኛ. በወቅታዊ የሠራተኞች ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፊ ዉይይት የተደረገ ሲሆን በም/ቤቱ የተነሡላቸዉን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የባንካችን ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ አቤ ሳኖ እና ም/ፕ የሰዉ ሃይል አስተዳደር የተከበሩ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ተገኝተዉ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ 2ኛ. እየተካሄደ ባለዉ አጠቃላይ የማህበሩ ምርጫ አፈጻጸም ላይ ተመክሮ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ 3ኛ. የ2015 እቅድ አፈጻጸም ተገምግሟል ፤ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ እና በጀት ፀድቋል፡፡ 4ኛ.ምክር ቤቱ ባንኩ ላደረገዉ የቦነስ እና የእርከን ጭማሪ ምስጋና እና እዉቅና የሰጠ ሲሆን ከኑሮ ዉድነቱ እና ሠራተኛዉ ሲጠብቀዉ ከነበረዉ የደመወዝ ክለሣ አንጻር በቂ ባለመሆኑ ጥያቄዉ መቀጠል እንዳለበት ወስኗል፡፡ 5ኛ. ለባንካችን እድገት እና ዉጤታማነት ሠራተኛዉ ተግቶ መስራት እንዳለበት እና ለደንበኞች አገልግሎት ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በአጠቃላይ ጉባኤዉ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማዉጣት ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን የአቋም መግለጫዉን ሙሉ ይዘት በሂደት ለሠራተኛዉ የምንገልፅ ይሆናል፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000