2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

ድጋፍ ዓይነት ስምንት

******************** ሠራተኛ ጡረታ ሲወጣ የሚደረግ ድጋፍ ይህ ድጋፍ የሚደረገዉ አባል ሠራተኛ ወይም የሥራ መሪ በጉብዝና ጊዜዉ ባንኩን ሲያገለግል ቆይቶ ጡረታ ሲወጣ ለዚህ አስተዋፅዖ ዕዉቅና ለመስጠት ታስቦ የሚደረግ ድጋፍ ነዉ፡፡ ይህ ድጋፍ የሥራ መሪ ከመሆናቸዉ በፊት የማህበሩ አባል ያልነበሩ ወይም አባልነታቸዉን በመሃል ላቋረጡ ሠራተኞች ጡረታ ሲወጡ አይከፈላቸዉም፡፡ የድጋፉ ዓይነት እና መጠን • የምስጋና ደብዳቤና የምስክር ወረቀት • በአባልነት እያሉ ጡረታ ለሚወጡ ሠራተኞች 15,000.00ብር • አባል የነበሩ እና ከሥራ መሪነት ጡረታ የሚወጡ ሠራተኞች 7,500.00 ብር መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች • ጡረታ ስለ መዉጣቱ የሚገልፅ ከባንኩ የሚሰጥ ማስረጃ • የጡረታ መታወቂያ ደብተር • ሁለት ጉርድ ፎሮግራፍ የጥያቄ አቀራረብ ሠራተኛዉ በአካል ወደ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀ ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡ የጊዜ ገደብ ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረዉ አባል ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ያለዉ የሥራ ግንኙነት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባለዉ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000