2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የውስጥ ስፖርት ውድድር ተጀመረ

የሰራተኞችን ማህበራዊ ትስስር ማጠናከርና ብቁና ጤናማ ሠራተኞችን ለማፍራት ዓላማ በማድረግ የሚከናወነዉ የዉስጥ ዉደድር ተጀምሯል፡፡ ከዉድድሩ መክፈቻ ቀደም ብሎ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሠራተኛ ማሕበሩና አና ከባንኩ የተወከሉ የስፖርት ዉድድሩ ኮሚቴ፤ የማሕበራችን ፕሬዝደንትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ለሁሉም ተወካይ በተገኙበት ስለ ዉድድሩ አካሄድ መግለጫ በመስጠት፣ የዲስትሪክቶች ዕጣ ድልድል እና የስፖርት ትጥቅ ሥርጭት ተደርጓል፡፡ ዉድድሩም ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የባንካችን ፕሬዝደንት እና ማኔጀመንት አባላት፤ የማሕበራችን ፕሬዝደንት እና ሥራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ፕሬዘዳንት እና ተወዳዳሪዎች ማለትም የአስሩ ዲስትሪክቶች፣ የዋናዉ መ/ቤት እና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች በተገኙበት ዉድድሩን በድምቀት የተከበሩ አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ከተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን አስጀምረዉታል፡፡ በዉድድሩ መክፈቻ ዕለትም ሁለት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን የዋናው መስሪያ ቤት ማኔጅመንት ቡድን ከ አራዳ እና የካ ዲስትሪክት ጥምረት ማኔጅመንት ቡድን ጋር ግጥሚያ አድርጎ ዋናው መስሪያ ቤት ማኔጅመንት ቡድን በአቶ አቤ ሳኖ መክፈቻ ጎል መምራት ቢችልም የአራዳ እና የካ ጥምረት ጎል በማስቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል። በሠራተኞች መካከል በተደረገዉ ጨዋታ ደግሞ የዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች ቡድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 6 ለ 2 የኮሜርሻል ኖሚኒስ ቡድንን ማሸነፍ ችሏል። ዉድድሩም ለ1 ወር ከ 15 ቀን የሚቆይ ሲሆን ዲስትሪክቶች እና የዋና መ/ቤት ሠራተኞችም በዉድድር ቦታዉ በመገኘት ዉድድሩን እንዲመለከቱ እና ድጋፍ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዉጪ ላሉ ዲስትሪክቶችም የስፖርት ትጥቅ ተመርቶ እንዳለቀ በቅርቡ የሚላክ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን! Telegram https://t.me/CBETUOfficial Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018 Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000