2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የድጋፍ ዓይነት ሰባት

አባል ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ ሥራ ከለቀቀ የሚደረግ ድጋፍ ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛ በማንኛውም ምክንያት በገዛ ፈቃዱ ከባንኩ ጋር ያለውን የሥራ ውል በቋሚነት ሲያቋርጥ የሚደረግ የመሸኛ ድጋፍ ነው፡፡ የድጋፍ መጠን • ከጀማሪ እስከ 3 ዓመት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ ምንም ድጋፍ አይደረግም • 3 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 2,000ሺ ብር ድጋፍ ይደረጋል • 4 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 2,500 ብር ድጋፍ ይደረጋል • 5 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 3,000ሺ ብር ድጋፍ ይደረጋል • 6 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 3,500 ብር ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡ መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች • የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ፣ • በገዛ ፈቃድ መልቀቁን የሚገልፅ ከባንኩ የተሰጠ ማስረጃ • የባንኩን መታወቂያ (ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ መታወቂያ) ኮፒ የጥያቄ አቀራረብ አባል ሠራተኛዉ በአካል ወደ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡ የጊዜ ገደብ ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረዉ አባል ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ያለዉ የሥራ ግንኙነት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡ ይቀጥላል…………. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000