2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

ማህበራችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገዉ ዉድድር የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ከህዳር 24 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገዉ ኢትዮጵያ የዓለም ስራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበት 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል እና ሀገር አቀፍ የአሰሪና ሠራተኛ ጉበዔ ማጠቃለያ ላይ ጥሩ አፈፃፀም ያላቸዉ አሰሪዎች እና የሠራተኞች ማህበራት ተሸልመዋል፡፡ ማህበራችንም የተረጋጋ እና ሠላማዊ እንዱስትሪ ግንኙነት ጠብቆ የሰራተኞችን መብት እና ጥቅም ከማስከበር አንፃር የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላትና 1ኛ በመዉጣት የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ይህ ዉጤት የሁላችንም የጋራ ጥረት ዉጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን! እያልን፤ በቀጣይም የባንካችንን ሰላም እና መረጋጋት ጠብቀን የሠራተኛዉን ምርታማነት ይበልጥ በመጨመር እና ለባንካችን እድገት እና ዉጤታማነት የድርሻችንን እየተወጣን የሠራተኛዉን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቃል እየገባን በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡ በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000