2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

*******ፓናል ዉይይት ተካሄደ*******

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር 55ኛ ዓመት (የግማሽ ክፍለ ዘመን) ጉዞ ክብረ በዓልና በሀገር ደረጃ ምቹ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጠርና ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲረጋገጥ በማድረግ የላቀ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ሠራተኛ ማሕበራት መካከል ተወዳድሮ አንደኛ በመሆን በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ የሆነበትን ኩነት በማስመልከት ፓናል ዉይይት አካሂዷል፡፡ በዕለቱም ለፓናል ዉይይቱ መግቢያ የሚሆን በማሕበሩ የ55 ዓመት ጉዞ ዉስጥ የነበሩ መልካም ተግባሮችና የገጠሙ ተግዳሮቶችን በተለያየ ጊዜ ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት የመሩ ባለታሪኮችን በሚያወሳ መልኩ ጥናታዊ ፅሁፍ በማሕበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አንተነህ ግርማ በኩል ቀርቧል፡፡ ፅሁፉም ከቀረበ በኋላ ወደ ፓናል ዉይይቱ የተገባ ሲሆን ፓናል ዉይይቱንም በፓናሊስትነት፡- ክቡር አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ኦላኒ ሴቃታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳይረክተሮች ቦርድ አባል አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ በርሀ የኢትዮጵያ ፋይናንስ ተቋማት ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና አቶ ካሳ ስዩም በአዲስ አበባ ከ/አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ሰላም ደህንነትና ጤንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የተሳተፉበት ሲሆን አቶ ግዛቸዉ አንማዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር የዋና መ/ቤት ተጠሪ/ጽ/ቤት ሰብሳቢ ደግሞ ፓናል ዉይይቱን በአወያይነት መርተዉታል፡፡ ከፓናል ዉይይቱ በተጨማሪ የቀድሞ የማሕበሩ ፕሬዝዳንቶችም ተሞክሯቸዉን አጋርተዋል፡፡በተለይም አቶ ኢታና ገለታ በማሕበሩ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ከሀገር እስከ መሰደድ የደረሱበትንና የከፈሉትን ዋጋ ከአዉስትራሊያ ሜልቦርን ድረስ መጥተዉ ለተወሰኑ አካላት ሲገልፁ መስማታችን ማሕበሩ ምን ያህል ዋጋ የተከፈለበት እንደሆነ ማሳያም ነበር፡፡ በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000