በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ 32 አባላትን የያዘ በተከበሩ ፕሮፌሰር መሀመድ አብዱ ሰብሳቢነት የተመራ ልኡክ ከባንካችን ፕሬዝዳንት እና የማኔጅመነት አባላት እንዲሁም የማህበራችን ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ዉይይት ተደርጓል፡፡ በዉይይቱም የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፡-የ6 ወር የባንኩ አፈፃፀም ዙሪያ ፤በባንኩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ፤በባንኩ የብድር አሰጣጥ ዙሪያ ፤በሰራተኛዉ ቅጥር ፤ዝዉዉር እና ሌሎችም አንኳር ጉዳዮች ጥያቄ ተነስቶ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል፡፡ በእለቱ ማህበራችን የተገኘዉን እድል በመጠቀም ለተወካዮች ምክር ቤት ልዑካን -ስለማህበራችን ታሪካዊ ዳራ በጥቂቱ ገለፃ ተደርጎላቸዋል -ማህበራችን ከባንኩ ጋር ስላለዉ መልካም ግንኙነትና ተግዳሮቶች ገለፃ ተደርጎላቸዋል በመጨረሻም ለተከበረዉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዑክ ማህበራችን ካነሳቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ በጥቂቱ -ከ Tax ጋር ተያይዞ ያለዉን ጉዳይ አፅንኦት እንዲሰጡ -በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ሰራተኞቻችን ደህንነታቸዉ አደጋ ዉስጥ ሆኖ በጦርነት መካከል በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሰራተኞቻችን ደህንነታቸዉ እንዲጠበቅ መንግስት የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡ -መንግስት ለንግድ ባንክ ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ከተነሱ ጥያቄዎች ጥቂቶቹ ሲሆኑ እነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ዉይይት ከተደረገ በኋላ ሰራተኛዉ የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን እንዳለበት አፅንኦት በመስጠት የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡