2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የቅርንጫፍ ጉብኝት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር የዲስትሪክት ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች ለአንድ ሳምንት ሲያካሄዱ የነበረ የቅርንጫፍ ጉብኝት በአብዛኘዉ ተጠናቋል፡፡ በጉብኝት እና ምልከታ ወቅትም የሠራተኛ ማህበሩ የዲስትሪክት ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች ከቅርንጫፍ ሠራተኞቹ ጋር ዉይይት ያከሄዱ ሲሆን ከሠራተኞቹም ሰፊ ጥያቄ እና አስተያየት ተነስቷል፡፡ ከሠራተኞቹ ለተነሱ ጥያቄዎችም በየደረጃ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በቅርንጫፍና በዲስትሪክት ደረጃ መፍትሄ እንዲያገኝ እየተደረገ ሲሆን፤በቅርንጫፍ ማነጀሮችና በዲስትሪክት ምላሽ ያልተሰጡ የሠራተኞችን ጥያቄ ለዋና መስሪያ ቤት ሠራተኞች ማህበር ተወካዮች እያሳዉቁ ይገኛሉ፡፡ ለአብነትም የቦሌ ዲስትሪክት ይጠቀሳል፡፡በቦሌ ዲስትሪክት በተካሄደዉ የማጠቃለያ ዉይይት ላይም የማህበራችን ፕሬዝደንትና ስራአስፈፃሚ ተገኝተዉ ከተወካዮች ጋር ዉይይት አካሄደዋል፡፡ በዕለቱም ማብራሪያ ለሚፈልጉ ጉዳዮች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በማህበሩ ደረጃ የማይፈቱ የሠራተኞችን ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንደሚሰጥም የማህበራችን ፕሬዝደንት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም የዲስትሪክት እና ቅርንጫፍ ተወካዮቹ የማህበራችን ፕሬዝደንትና ስራአስፈፃሚዎች የሠራተኞችን ጥያቄ ለማዳመጥ ስለተገኙ በማመስገን የዕለቱ ዉይይት ተጠናቋል፡፡ ለበለጠ መረጃ ከታች ያሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ ይከታተሉ Telegram https://t.me/CBETUOfficial Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018 Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ስልክ፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000