2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

ማሕበራችን ለአባል ሠራተኞቹ የሚያደርጋቸዉ የድጋፍ ዓይነቶች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ከባንኩ ጋር በሚያደርጋቸዉ ድርድሮች የሁሉንም የአባል ሠራተኞችን መብት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከማስከበር ባሻገር አባላት ችግር ሲደርስባቸዉ ከጎናቸዉ መቆም አስፈላጊ በመሆኑ፤አባል ሠራተኞች ከማህበራቸዉ የሚጠብቁት ፋይዳ እየሰፋ እና እየጨመረ ስለመጣ ከሌሎች አባል ካልሆኑ ሠራተኞች በተለየ መልኩ አባል በመሆናቸዉ ብቻ ከማህበሩ የሚያገኙት የተለያየ ጥቅም መኖር ስላለበት፤እንዲሁም የማህበሩ ተደራሽነት ለመስፋት እና አባሎቹ ማህበሩ ላይ ያላቸዉ እምነት መጎልበት ስላለበት በማህበራችን ሕገ ደንብ መሠረት የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይህ የአባላት ድጋፍ መመሪያ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡ የመመሪያዉ ተፈፃሚነት ወሰን ይህ የአባላት ድጋፍ መመሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር አባላት ላይ ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ሲሆን፤ የተወሰኑ የድጋፍ ዓይነቶች በድጋፍ ዓይነቱ ትርጉም ስር በተቀመጠዉ መሠረት አባል ያልሆኑ ሠራተኞችን እና የሥራ መሪዎችንም ሊመለከት ይችላል፡፡ አንድ ድጋፍ የሚጠይቅ አባል ሠራተኛ ማሟላት ያለበት መስፈርት፡፡ -የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣ -የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ እና ማህበሩ ላይ ማናቸውንም አሉታዊ ድርጊቶች ፈጽሞ የማያውቅ፣ -በተጨማሪም ማህበሩ አስፈላጊ ናቸዉ ብሎ ያመነባቸውን ሌሎች ማስረጃዎችን ማቅረብ መቻል አለበት፤ የድጋፍ ዓይነት፡- 1.የታካሚ መጠየቂያ -ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ ከአንድ ወር በላይ ታሞ ከተኛ በተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች የሚፈፀም የመጠየቂያ ድጋፍ አይነት ነዉ፡፡ -ይህ ድጋፍ ታሞ ለተኛ አባል ሠራተኛ የሚከፈል ሳይሆን ለጥየቃ የሚሄዱ ባልደረቦች ባዶ እጃቸዉን እንዳይሄዱ ቢያንስ ፍራፍሬ ገዝተዉ እንዲጠይቁ ማድረጊያ ሲሆን መጠኑም 2,000 ብር ነዉ፡፡ አባል ሠራተኛዉ ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች -የሕክምና ፈቃድ ላይ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ከህክምና ተቋምና ከባንኩ -እንዲሁም የባንኩን መታወቂያ ኮፒ የጥያቄ አቀራረብ -ታማሚዉ ወይም ቤተሰቡ ወይም የቅርንጫፍ/የክፍሉ ሠራተኛ ተወካይ ለተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላት ጥያቄ ያቀርባሉ፣ -የተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ጉዳዩን በማጣራት በራሳቸዉ ወይም በቅርንጫፍ/ክፍሉ ተወካይ መሠረት ድጋፉ ለሠራተኛዉ እንዲደርስ ይደረጋል፤ የጊዜ ገደብ ድጋፉ የታካሚ መጠየቂያ ስለሆነ አንድ አባል ሠራተኛ ሕክምናውን ጨርሶ ወደ ሥራ ገበታው ከተመለሰ በኋላ ሊጠይቅ አይችልም፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000