2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የድጋፍ ዓይነት ሁለት፡-

ለውጭ ሀገር ሕክምና የሚደረግ ድጋፍ ይህ ድጋፍ አባል የሆነ ሠራተኛ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ በሚታከምበት ወቅት ድርጅቱ/ባንኩ ከሚሰጠው የሕክምና ወጪ 20,000 ዶላር በተጨማሪ ታካሚው ተጓዳኝ ጥቃቅን ወጪዎችን እንዲሸፍንበት በማሕበሩ የሚደረግ ድጋፍ አይነት ነዉ፡፡ የድጋፍ መጠን • ድጋፉ የሚደረገዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በአንድ ጊዜ የሚከፈል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) • ድጋፉ የሚደረገዉ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በአንድ ጊዜ የሚከፈል ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሲሆን በጥቅሉ 75,000 ብር ይደገፋል ወይም ይደጎማል፡፡ ድጋፍ የሚጠይቅ አባል ሠራተኛ ማሟላት ያለበት መስፈርቶች • የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣ • የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ እና ማህበሩ ላይ ማናቸውንም አሉታዊ ድርጊቶች ፈጽሞ የማያውቅ፣ • በተጨማሪም ማህበሩ አስፈላጊ ናቸዉ ብሎ ያመነባቸውን ሌሎች ማስረጃዎችን ማቅረብ መቻል አለበት፤ • ሠራተኛዉ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ እንዲታከም በሀኪሞች ቦርድ የተረጋገጠበት የህክምና ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለበት፤ • ባንኩ ለውጭ ሀገር ሕክምና ክፍያ የፈጸመበት ሰነድ ወይም የውጭ ምንዛሪ የተፈቀደበት ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለበት፤ • የሚሄዱበት ሀገር ቪዛ እና የባንኩ መታወቂያ ኮፒ፣ የጥያቄ አቀራረብ ሠራተኛዉ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን በማሟላት የማህበሩ ጽ/ቤት በአካል ወይም ህጋዊ ወኪል በመቅረብ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡ የጊዜ ገደብ ይህን ድጋፍ መጠየቅ የሚቻለው ህክምናው ከመጠናቀቁ በፊት ወይም የህክምና ማስረጃው ከተሰጠ በኋላ እስከ 6 ወራት ባለዉ ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000