2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የድጋፍ ዓይነት ሦስት፡

በህመም ፈቃድ ምክንያት ደመወዝ ለተቋረጠበት አባል የሚደረግ ድጋፍ ————————————————————————————- ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ በሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከተኛ እና ወደ ሥራዉ መመለስ ባለመቻሉ ባንኩ የሠራተኛዉን ደመወዝ እየቆራረጠ የሚያስቀረዉን መጠን ማህበሩ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የሚሸፍነዉ የድጋፍ ዓይነት ነዉ፡፡ በተጨማሪም አባል ሠራተኛዉ ወይም የሥራ መሪ በሕመሙ ምክንያት ወደ ሥራ የማይመለስ ከሆነ ለአንድ ጊዜ የሚደረግ ድጋፍን ይጨምራል፡፡ የድጋፍ መጠን ሀ. አባል ሠራተኛዉ በህመም ከሥራዉ ከተስተጓጎለበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የሚዘልቅ ሆኖ ባንኩ የሠራተኛዉን ደመወዝ 1/2ኛ፣ 1/3ኛ እና 2/3ኛ እያለ ወይም በሌላ ስሌት ቆርጦ የሚያስቀረዉን መጠን ማህበሩ የሚሸፍን ይሆናል፡፡ ለ. በዚህ አንቀፅ ከላይ የተጠቀሰዉ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ከአንድ ዓመት በኋላም አባል ሠራተኛዉ በሕመሙ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ወደ መደበኛ ሥራዉ የማይመለስ ከሆነ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብር ድጋፍ ይደረጋል፡፡ ከላይ አንቀፅ (ለ) የተጠቀሰዉ ድጋፉ ለሥራ መሪ ከሆነ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ይሆናል፡፡ አባል ሠራተኛዉ ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች •የህመም ፈቃድ ከባንኩ ከሚመለከተው ክፍልና ጤና ተቋም ማስረጃ ማቅረብ፣ • የምስክር ወረቀት ከታወቀ የህክምና ተቋም፣ • ባንኩ ይከፍለው የነበረው ሙሉ ደመወዝ እና ከተቆረጠበት በኋላ እየተከፈለው ያለውን የደመወዝ መጠን የሚገልጽ ፔሮል ወይም ደብዳቤ፣ • ወደ ሥራ መመለስ የማይችል ከሆነ ይህንኑ የሚገልፅ ሙሉ የህክምና ማስረጃ፣ • የባንኩን መታወቂያ ኮፒ የጥያቄ አቀራረብ • ሠራተኛዉ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን በማሟላት የማህበሩ ጽ/ቤት በአካል ወይም ህጋዊ ወኪል በመቅረብ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የጊዜ ገደብ አንድ አባል ሠራተኛ ይህንን መብቱን መጠየቅ የሚችለዉ ችግሩ ከደረሰበት ወይም ከሥራዉ ከተስተጓጎለበት ጊዜ አንስቶ ባንኩ ሙሉ ደመወዙን መክፈል ካቋረጠበት ቀን እስከ 3 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ብቻ እስከ 6 ወራት የይርጋ ጊዜዉ ሊራዘም ይችላል፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000