2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የድጋፍ ዓይነት አራት፡

ማረሚያ ቤት ለሚቆይ አባል የሚደረግ ድጋፍ ይህ ድጋፍ አንድ አባል ሠራተኛ በማንኛዉም ምክንያት ከታሰረ ወይም ማረሚያ ቤት ከቆየ የሚደረግ ድጋፍ ነዉ፡፡ ይህ ድጋፍ ለአንድ አባል ሠራተኛ ሊሰጥ የሚችለዉ በሦስት ዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ፡፡ የድጋፍ ዓይነት እና መጠን ሀ. የሕግ ድጋፍ ማህበሩ በጽ/ቤቱ ቀጥሮ የሚያሰራዉን ወይም ሌላ የሕግ ባለሙያ በመጠቀም የሕግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለ. የገንዘብ ድጋፍ፡ ሠራተኛዉ ለፍ/ቤት ክርክርም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ሊያዉለዉ የሚችል፡- • ከ15 ቀን እስከ 30 ቀን ለታሰረ አባል ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) መጠየቂያ፣ • ከ አንድ ወር በላይ እስከ ሦስት ወር ለታሰረ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) እና • ከሦስት ወር በላይ ለታሰረ አባል ሠራተኛ ተጨማሪ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ይከፈላል፡፡ አባል ሠራተኛዉ ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች • የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣ • የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ እና ማህበሩ ላይ ማናቸውንም አሉታዊ ድርጊቶች ፈጽሞ የማያውቅ ሆኖ፣ • መታሰሩን እና ማረሚያ ቤት የቆየበትን ጊዜ የሚገልፅ የፖሊስ ማስረጃ • መታሰሩን እና ማረሚያ ቤት የቆየበትን ጊዜ በማስመስከር ሦስቱ የቅርንጫፍ/የክፍል ተወካዮች የፈረሙበት እና የቅርንጫፉ ማህተም ያረፈበት ማስረጃ • የባንኩ መታወቂያ ኮፒ የጥያቄ አቀራረብ • ጥያቄዉ የቀረበዉ አባል ሠራተኛዉ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ ከሆነ ሠራተኛዉ እራሱ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ ሞልቶ ጥያቄዉን ያቀርባል፤ • ጥያቄዉ የቀረበዉ አባል ሠራተኛዉ ማረሚያ ቤት እያለ ከሆነ ግን ቤተሰቡ ወይም የቅርንጫፍ/የክፍል ተወካዮች ለተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ያሳዉቃሉ፤ • የተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ጉዳዩን ካጣሩ በኋላ መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች እንዲሟሉ ያደርጋሉ፤ • ክፍያዉ የ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ከሆነ በተጠሪ ጽ/ቤት ደረጃ ይፈፅማሉ፤ • ክፍያዉ ከ1000 (አንድ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ በሸኚ ደብዳቤ በመደገፍ ለማህበሩ ጽ/ቤት ይላካል የጊዜ ገደብ የዚህ ድጋፍ ጥያቄ አባል ሠራተኛዉ ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ መቅረብ የሚችል ሆኖ ሠራተኛዉ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ በማንኛዉም ሁኔታ ከ3 ወራት በላይ ከቆየ ተቀባይነት የለዉም፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000