2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የድጋፍ ዓይነት አምስት

አባል ሠራተኛ በጊዜያዊነት ከሥራ ከታገደ የሚደረግ ድጋፍ ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ በማንኛዉም ምክንያት ከመደበኛ ሥራው በሚታገድበት ወቅት የሚደረግ ድጋፍ ሆኖ ይህ ድጋፍ ሊደረግ የሚችለዉ ሠራተኛዉ ማረሚያ ቤት በመቆየት ምክንያት ድጋፍ ያልተደረገለት ከሆነ ብቻ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ይህ ድጋፍ ለአንድ አባል ሠራተኛ ሊሰጥ የሚችለዉ በሦስት ዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ፡፡ የድጋፍ ዓይነት እና መጠን ሀ. የሕግ ድጋፍ፡ ማህበሩ በጽ/ቤቱ ቀጥሮ የሚያሰራዉን ወይም ሌላ የሕግ ባለሙያ በመጠቀም የሕግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለ. የገንዘብ ድጋፍ፡ ዕግድ የሚቆየዉ ለአንድ ወር ብቻ በመሆኑ ሠራተኛዉ ለፍ/ቤት ክርክርም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ሊያዉለዉ የሚችል • ከ15 ቀን እስከ 45 ቀን ለታገደ ብር 3,000 (ሦስት ሺህ ብር) እና • ከ45 ቀን በላይ ለታገደ አባል ሠራተኛ ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር) ይከፈላል፡፡ መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች • የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣ • የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ • ከባንኩ የተሰጠው የእግድ ደብዳቤ፣ • ከእግዱ በኋላ በባንኩ የተሰጠው የውሳኔ ደብዳቤ፡ ማለትም ወደ ሥራ የተመለሰበት ወይም የተሰናበተበት ወይም ውሳኔ ያልተሰጠዉ እና ዕግድ ላይ ያለ መሆኑን የሚገልፅ የባንኩ ወይም የፍ/ቤት ማስረጃ • የባንኩ መታወቂያ ኮፒ (ወደ ባንኩ የተመለሰ ከሆነ ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ መታወቂያ) የጥያቄ አቀራረብ አባል ሠራተኛዉ በተጠሪ ጽ/ቤቶች ወይም በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በአካል በመገኘት/ህጋዊ ወኪል እና መስፈርቶችን በማሟላት ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀ የድጋፍ መጠየቂያ ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡ ጥያቄዉ የቀረበዉ ለተጠሪ ጽ/ቤቶች ከሆነ በሸኚ ደብዳቤ ወደ ዋናዉ የማህበሩ ጽ/ቤት ይልካሉ፤ ክፍያዉ የሚፈፀመዉ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ነዉ፡ የጊዜ ገደብ የዚህ ድጋፍ ጥያቄ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ መቅረብ የሚችል ሆኖ ሠራተኛዉ ወደ ሥራ ከተመለሰ በኋላ በማንኛዉም ሁኔታ ከ3 ወራት በላይ ከቆየ ተቀባይነት የለዉም፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000