2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የድጋፍ ዓይነት ስድስት

አባል ሠራተኛ ከሥራ ከተሰናበተ የሚደረግ ድጋፍ ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ ከራሱ ፈቃድ ውጪ ማለትም በባንኩ ዉሳኔ ከሥራ እንዲሰናበት ከተደረገ የሚሰጥ የስንብት ክፍያ ነዉ፡፡ የድጋፍ መጠን 1. ሠራተኛዉ ታስሮ ወይም ታግዶ በነበረ ጊዜ ድጋፍ ተደርጎለት ከሆነ • ከጀማሪ እስከ 3 ዓመት 3,000.00 ብር • ከ3 በላይ እስከ 7 ዓመት 5,000.00 ብር • ከ7 በላይ እስከ 15 ዓመት 10,000.00 ብር • ከ15 ዓመት በላይ 15,000.00 ብር 2. ሠራተኛዉ በመታሰር ወይም በመታገድ ምክንያት ምንም የገንዘብ ድጋፍ ያልተደረገለት ከሆነ • ከጀማሪ እስከ 3 ዓመት 7,000.00 ብር • ከ3 በላይ እስከ 7 ዓመት 10,000.00 ብር • ከ7 በላይ እስከ 15 ዓመት 15,000.00 ብር • ከ15 ዓመት በላይ 20,000.00 ብር መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች • የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣ • የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ • ከባንኩ ስለ መሰናበቱ የሚገልፅ ከባንኩ የተሰጠ ማስረጃ • መታወቂያ ኮፒ (ወደ ባንኩ የተመለሰ ከሆነ ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ መታወቂያ) የጥያቄ አቀራረብ ሠራተኛዉ በአካል ወደ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀ ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡ የይርጋ ጊዜ ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረዉ አባል ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ያለዉ የሥራ ግንኙነት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 2 ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡ ይቀጥላል………….

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000