2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

ድጋፍ ተደረገላቸዉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ለክበብ ሠራተኞች ድጋፍ አደረገ፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የክበብ ሠራተኞች በእጅግ ዝቅተኛ ደመወዝ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ መሆናቸዉን ከግንዛቤ በማስገባት በቂ ባይባልም ለበዓል ጥቂትም ነገር ቢሆን ወጪ እንዲሸፍን በማሰብ የተዘጋጀ ድጋፍ ነዉ፡፡ በዚህም መሠረት ክበቡን ከ 30 ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች 15ሺ ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ ከ 20 ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች 10 ሺ ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ከ 15 ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች 5ሺ ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የዚህ ድጋፍ ዋናዉ ዓላማ ሠራተኛ ማሕበሩ ማሕበራዊ ሃላፊነት መወጣት እና የክበብ ሠራተኞቹ በክበባቱ የሚጠቀሙ የባንኩን ሠራተኞች ደስተኛ ሆነዉ እንዲያገለግሉ ማበረታቻ እንዲሆን ያለመ ነዉ፡፡ በዕለቱም የማሕበራችን ፕሬዝደንት እና ሥራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዉ ለክበብ ሠራተኞች ይህንን ድጋፍ እና እዉቅና የሰጡ ሲሆን አጠቃላይ በ 7 ክበባት የሚሰሩ ከ 136 በላይ ሠራተኞች የድጋፉ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ በመጨረሻም የክበባት ሠራተኞቹም ይህ ድጋፍ አዲስና ከዚህ በፊት ተደርጎላቸዉ የማያዉቁት በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልፀዉ አመስግነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000