2176 0906570000 tradeunion@cbe.com.et

News

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር የ2015 ዓ.ም የአጠቃላይ የምርጫ ዝግጅት ተጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር በ2015 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ በዚሁ አግባብ በ61ኛዉ የም/ቤት ስብሰባ የተመረጡት የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፡- • የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴዉ የሚያከናዉናቸዉ ዝርዝር ተግባራት ላይ ዉይይት እና ስልጠና ተሰጥቷል • በምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራር በተዘጋጀዉ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሰነድ (Guide line) ላይ ዉይይት ተደርጓል • ለምርጫዉ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች እንዲሟሉ ተደርጓል እንዲሁም • የምርጫ አስፈጻሚዎች ምደባ እና ስምሪት ተከናዉኗል፡፡ በመሆኑም ከፊታችን ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቅርንጫፎች እና ወደ ስራ ክፍሎች በመሄድ የሰራተኛ ተወካዮች ምርጫ የሚካሄድ ስለሆነ የማህበራችን አባላት ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ማንኛዉም ጥያቄ ካለ በ8679 በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Get In Touch

2176

tradeunion@cbe.com.et

0906570000